The Pentateuch Genesis

Joseph's Brothers in Egypt

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Seed Genesis 41-42 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 22 ከ730
ማውረዶች

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Genesis 41:16

“Joseph answered Pharaoh. ‘It is God who will give Pharaoh a favorable answer.’”

ዮሴፍ ወደ ስኬት ማማ በወጣበት ጊዜ፥ ምልከታዉን እና አትኩሮቱን ሁሉ ወደ ልዑል እግዚዓብሔር አደረገ። በሁሉም ቦታ ላይ ስለ ጥበብ እና መረዳት በሚያወራበት ጊዜ የሚያነሳዉ ዋና ሃሳብ፥ እግዚዓብሔር ነዉ። ከራሱ በላይ ያመላከተዉ እግዚዓብሔርን ነው! ሙገሳ እና ዋጋ ከሰዉ ዘንድ ለራሱ አልተቀበለም።

እግዚዓብሔር በሁሉም ነገር ዉስጥ እንደሚገኝ እና ዓለም በሞላ በእርሱ እንደተያያዘ አስታዉስ! ትከሻህን ከፍ አድርገህ፥ ሞገስን ለራስህ ትወስዳለህ? ወይስ ሁሉም ነገር የሚመጣዉ ከእግዚዓብሔር እንደሆነ ታስታዉሳለህ? ዛሬ፥ ሁሉንም ክብር እና ምስጋና ለእግዚዓብሔር ስጥ!

"ዮሴፍም ለፈርዖን እንዲህ ብሎ መለሰ፦ ይህ በእኔ አይደለም፤ እግዚአብሔር ግን ለፈርዖን በደኅንነት ይመልስለታል።"

ኦሪት ዘፍጥረት 41:16

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ኦሪት ዘፍጥረት 42:18፦ "በሦስተኛውም ቀን ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፦ ትድኑ ዘንድ ይህን አድርጉ፤ እኔ እግዚአብሔርን እፈራለሁና።"

የያዕቆብ መልዕክት 1:17፦ "በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።"

ወደ ቆላስይስ 1:17፦ "እርሱም ከሁሉ በፊት ነው ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል።"