The Pentateuch Genesis

God Blesses Joseph In Everything He Did

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Seed Genesis 39-40 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 21 ከ730
ማውረዶች

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Genesis 39:21

“But the LORD was with Joseph and extended kindness to him. He granted him favor in the eyes of the prison warden.”

እግዚዓብሔር ከዮሴፍ ጋራ ስለነበረ፥ ለሥራዉ መከናወንን ሰጠዉ። ዮሴፍ በጌታዉ በጶጢፋራ ዘንድ ሞገስ አገኘ፥ እርሱም የራሱ በሆነ ነገር ሁሉ ላይ ሾመዉ። ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ በታሰረ ጊዜም፥ በጠባቂዎቸ ዘንድ ዮሴፍ ሞገስን አግኝቷል። በህይወት ከፍታ ላይ ወይም ዝቅታ ላይ ቢሆንም፥ እግዚዓብሔር ከዮሴፍ ጋራ ነበር። ዮሴፍ በሁሉ ሁኔታ ወስጥ በእግዚዓብሔር ፀንቷል።

በማንኛዉም ስፍራ ላይ ብትሆን፥ እግዚዓብሔር ከአንተ ጋራ እንደሚሆን የተስፋ ቃል ገብቷል። ዛሬ ስሜቶችህን በሁኔታዎች ላይ አታስደግፈዉ! እርሱ በአንተ ደስ ይለዋል! ለህይወትህም ዓላማ አለዉ!

"እግዚአብሔርም ከዮሴፍ ጋር ነበረ፤ ምሕረትንም አበዛለት፥ በግዞት ቤቱም አለቃ ፊት ሞገስን ሰጠው።"

ኦሪት ዘፍጥረት 39:21

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ትንቢተ ሶፎንያስ 3:17፦ "አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው፤ በደስታ በአንቺ ደስ ይለዋል፥ በፍቅሩም ያርፋል፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል ይባላል።"

መዝሙረ ዳዊት 139:7-10፦ "ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ? ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ። እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥ በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች።"

ትንቢተ ኢሳይያስ 26: 3-4፦ "በአንተ ላይ ታምናለችና በአንተ ለምትደገፍ ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ። ጌታ እግዚአብሔር የዘላለም አምባ ነውና ለዘላለም በእግዚአብሔር ታመኑ።"