The Pentateuch Genesis

The Sons Of Jacob

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Seed Genesis 38 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 20 ከ730
ማውረዶች

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Genesis 38:26

“Judah recognized them and said, ‘She is more in the right than I, since I did not give her to my son Shelah.’ And he did not know her intimately again.”

የይዳን እና የትዕማርን ታሪክ ስናነብ፥ የመሲሁ ዘር እንዲቀጥል የተሰበሩ ሰዎችን እንደሚጠቀም እናያለን። ምንም እንኳ ሁለቱም ሓጥያት ቢሰሩ፥ እግዚዓብሔር ግን ተጠቅሞባቸዋል! የይሁዳ ወንድም የሆነዉን፥ ዮሴፍ፥ የከርቶስን ዘር ለመሸከም፥ በትልቅ የህይወት ታሪክ ዉስጥ እግዚዓብሔር አለመጠቀሙ የሚደንቅ ነው።

በህይወትህ ለብዙ ነገር እንደማትበቃ የሚሰማህ ከሆነ፥ ወይም ብዙ ስህተቶች ካሉብህ፥ እግዚዓብሔር የሚሠራዉን እንደሚያዉቅ አስታዉስ! እግዚዓብሔር ለፈቃዱ እና ለክብሩ የማንኛዉም ሰዉ ታሪክ ሊጠቀም ይችላል። እርሱ የእምነታችን ፈፃሚ ነው! እግዚዓብሔር ዛሬ ይጠቀምሃል።

"ይሁዳም አወቀ፦ ከእኔ ይልቅ እርስዋ እውነተኛ ሆነች፤ ልጄን ሴሎምን አልሰጠኋትምና አለ። ደግሞም አላወቃትም።"

ኦሪት ዘፍጥረት 38:26

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ትንቢተ ኢሳይያስ 43:7፦ "ሰሜንን፦ መልሰህ አምጣ፥ ደቡብንም፦ አትከልክል፤ ወንዶች ልጆቼን ከሩቅ ሴቶች ልጆቼንም ከምድር ዳርቻ፥ በስሜ የተጠራውን ለክብሬም የፈጠርሁትን፥ የሠራሁትንና ያደረግሁትን ሁሉ አምጣ እለዋለሁ።"

ወደ ዕብራዉያን 12:2-3፦ "እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና። በነፍሳችሁ ዝላችሁ እንዳትደክሙ፥ ከኃጢአተኞች በደረሰበት እንዲህ ባለ መቃወም የጸናውን አስቡ።"

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:9፦ "እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ።"