The Pentateuch Genesis

Problems With Being In The World

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Seed Genesis 19 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 8 ከ730
ማውረዶች

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Genesis 19:29

"So it was, when God destroyed the cities of the plain, He remembered Abraham and brought Lot out of the middle of the upheaval when He demolished the cities where Lot had lived."

የሰዶም እና የገሞራ ሰዎች ራሳቸዉን ለፍትወታቸዉ አሳልፈዉ እንደሰጡ፤ በእግዚዓብሔር ላይ ባለመደገውፍ ስጋዊ ድርጊትን ፈፀሙ። እግዚዓብሔር ሎጥን አዳነዉ፥ ነገር ግን አንድን ከተማ በሙሉ አጠፋ! የእኛ ትዉልድ በተመሳሳይ አያሌ መንገዶች: በእግዚዓብሔር ላይ ሙሉ በሙሉ ባለመደገፍ እንደ ሰዶም እና ገሞራ ራሱን ለፈተናዎች አሳልፎ በመስጠት፥ ስጋዊ ህይወትን መኖር ቀትሏል። ይመስገነዉና፥ ኢየሱስ እያንዳንዳችንን አድኖናል! ይህም በሞቱ፥ በቀብሩ፥ በትንሳኤዉ እና በመንፈስ ቅዱስ ስጦታዉ የሆነ ፀጋዉ እና ምህረቱ ነው።

ዛሬ፥ ስለፀጋዉ እና ምህረቱ ለእግዚዓብሔር ምስጋና ስጡ። "ክርስቶስን ደስ የሚያሳኝ ህይወት እየኖርኩ ነው ወይስ ለስጋዬ ምኞት እና ለፈተናዎች ራሴን አሳልፌ እየሰጠሁ ነው?" ብላችሁ ራሳችሁን ጠይቁ። ይህ ትዉልድ የእግዚዓብሔርን ፊት የሚፈልግ ትዉልድ ይሁን!

"እነሆ ባሪያህ በፊትህ ሞገስን አግኝቶአል፥ ነፍሴን ለማዳን ያደረግህልኝን ምሕረትህንም አብዝተሃል፤ ክፉ እንዳያገኘኝና እንዳልሞት ወደ ተራራ ሸሽቼ አመልጥ ዘንድ አልችልም፤"

ኦሪት ዘፍጥረት 19:29

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ወደ ቲቶ 3:3፦ "እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።"

ወደ ቲቶ 3:5-7፦ "እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤ ያን መንፈስም፥ በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፥ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው።"

መዝሙረ ዳዊት 24:3-6፦ "ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ይወጣል? በቅድስናውስ ስፍራ ማን ይቆማል? እጆቹ የነጹ፥ ልቡም ንጹሕ የሆነ፥ ነፍሱን ለከንቱ ያላነሣ፥ ለባልንጀራውም በሽንገላ ያልማለ። እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ በረከትን ከመድኃኒቱ አምላክም ምሕረትን ይቀበላል። ይህች ትውልድ እርሱን የምትፈልግ ናት፥ የያዕቆብን አምላክ ፊት የምትፈልግ።"